News News
Minimize Maximize
« Back

የሚታቀዱ ዕቅዶች የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንዳለባቸው ተገለፀ

   

የሚታቀዱ ዕቅዶች የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ቅንጅታዊ አሰራርን መከተል እንዳለባቸው ተገለፀ

በየደረጃው የሚታቀዱና የሚሰሩ የሪፖርት ሥራዎች የባለድርሻ አካላትን ተሣትፎ እና ቅንጅታዊ አሠራር መከተል እንዳለባቸው ተገለፀ። የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ለፌደራል ለተጠሪ ተቋማት ለክልል እና ለከተማ አስተዳደር የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ አመራሮች እና ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረውን የሦስት ቀናት ግሞገማዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል

 

በባለፉት ሁለት ቀናት በእቀድ አስተቃቀድና በሪፖርት ዝግጅት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በዛሬው ግምገማዊ ስልጠና ደግሞ ስለ ሞዴል ዕቅድ አስተቃቀድ እና በሪፖርት አደራረግ ዙሪያ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል።

 

ሁለቱንም ስልጠናዎች የሰጡት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ከፍተኛ ባለሙያዎች አቶ ዘነበ መኮነን እና አቶ ክንፈሚካኤል ተስፋዬ የሚታቀዱ ዕቅዶችና የሚዘጋጁ ሪፖርቶች ገላጭ በሆኑና የዕቅድ አስተቃቀድ እንዲሁም የሪፖርት አደራረግ መስፈርቶችን ባሟሉ መንገድ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

 

አቶ ክንፈሚካኤል አያይዘውም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚያዘጋጇቸው ሪፖርቶች በጋራ በፀደቀው የመግባቢያ ሰነድ መሠረት መሆን እንዳለበት ተናግረዋል። ተሳታፊዎችም በቀረቡት ሰነዶችና በነበረው ግምገማዊ ስልጠና ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይም ማጠቃለያ የሰጡት የዕቀድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ኃላፊው አቶ ደረጀው ባይጨክን አማካኝነት ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል

 

በመጨረሻም በፕሮግራም መዘጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወይዘሮ መሠረት መስቀሌ ዕቀድ በዋናነት የሥራ ዓላማን ለማሣካትና ከግብ ለማድረስ እጅግ ወሳኝ የሆነ የልማትና የአመራር መሳሪያ ነው ያሉት ሲሆን የዕቅድ አዘጋጃ የተቋምን ርዕይና ተልዕኮን አመላክቶ ዓላማና ግቦችን ለማሳካት በእቅዱ ዙሪያ የጋራ አመለካከት በመፍጠር አሳታፊና አቅጣጫ አመላካች ሆኖ ካለው ተጨባጭ የለውጥ

ሂደት ጋር የሚከለስና የሚሻሻል ገፅታዎች ሊኖሩት ይገባል ብለዋል።

የዜናና ፎቶ ጥንቅር :- ጌታቸው ኃይሉ