News « Back የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና የሶማሌ ክልላዊ መንግስት 8ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡየአትዮጵያ ከተሞች ፎረም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስተባባሪነት በየሁለት አመቱ ይካሄዳል ፡፡ ፎረሙ መካሄድ ከጀመረ ዘጠኝ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም ሰባት ከተሞች የአዘጋጅነት እድል አግኝተዋል፡፡ ዘንድሮ ፎረም ለ8ተኛ ጊዜ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት ዋና ከተማ ጅግጂጋ “መደመር ለኢትዮጵያ ከተሞች ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 9 ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለተከታታይ ሰባት ቀናት በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን የፎረሙን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ በተመለከተ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እና የፎረሙ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ካሳሁን ጎፌ እንዲሁም የሶማሌ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አብድልፈታ ሼህ ቢህ በተገኙበት ጥር 15 ቀን 2011ዓ.ም ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በሶማሌ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር አብድልፈታ ሼህ ቢህ በበኩላቸው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ከ95% በላይ መጠናቀቃቸውን ጠቅሰው የክልሉ ሰላም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ እና የሠላሙ ጠባቂ እራሱ ህብረተቡ በመሆኑ ከህብረተሰቡ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ውይይት ተደርጓል፡፡ ስለዚህ የከተማው ህብረሰብ የሚመጡ እንግዶችን ደህንነት ለመጠበቅ ግንባር ቀደም ተሳተፊ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ አክለውም ጅግጅጋ ሶማሌ ክልልን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጺያዊ እንግዳ አቀባበልን በሚመጥን መልኩ እንግዶቹን ለመቀበል ኢትዮጺያን ወክላ ስለተዘጋጀች መጥታችሁ እንድትጎበኙን የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡ በፎረሙም ከ200 በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያና ከ10 በላይ የሚሆኑ የጎረቤት ሀገር እህት ከተሞች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
|