በቀጣይ ዓርብ ነሐሴ 27/2008 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ሁሉም የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች፣የስራ ሂደት መሪዎችና አመራሮች በተገኙበት የበጀት ዓመቱን የእቅድ አፈፃፀም እንደሚገመግም አስታወቀ፡፡
የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ካሳ ወዳጅ እንዳሉት የግምገማው ዋና ዓላማ የ2008 በጀት ዓመት እቅድ የስራ አፈፃፀም በጽ/ቤት ደረጃ በመገምገም በጥንካሬ ያሉ መልካም ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና በአፈፃፀም በኩል ውስንነት የተስተዋለባቸው የቀጣይ የእቅድ አካል ሆነው ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንዲሰሩ ለማድረግ ተስቦ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
በሌላ በኩል የጽ/ቤት ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የግምገማ መድረኩ በጽ/ቤቱ ስር ያሉ የሁሉም የስራ ሂደቶች፣ደጋፊ የስራ ሂደቶችና የስራ ክፍሎችን ሪፖርቶች በአንድ ተጠቃለው በጽ/ቤት ደረጃ እንደሚያቀርቡት ተናግረዋል ፡፡
የግምግማ ፕሮግራሙ በባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዳራሽ እንደሚያካሄድ፣ የአንድ ቀን ቆይታ እንደሚኖረውና እንዲሁም ለመድረኩ የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የኮ/ጉ/ደ/የስራ ሂደት