MUI_gallery
Minimize Maximize
MUDC_gallery is temporarily unavailable.
Web Content Display Web Content Display
Minimize Maximize

 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የኩሙርክ ወረዳ የሆራዛብ ከተማ፣ የመንጌ ከተማና የሆሞሻ ከተማ  መሰረታዊ ፕላን ርክክብ አደርጓል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ  የሆራዛብ ከተማ፣ የመንጌ ከተማና የሆሞሻ ከተማን መሰረታዊ ፕላንን ሲሰሩ ቆይቶ ህብረተሰቡን ማወያየታቸው ይታወሳል፡፡ በመሆኑም በውይይቱ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን ጨምሮ ስራውን አጠናቆ ለሚመለከተው አካለት አስረክቧል፡፡የሆራዛብ ከተማ ፕላን የቅየሳው ስራው በ2011 በጀት አመት የተጀመረ ሲሆን በ2013 በጀት አመት 50 ያህል ብሎኮች ተከፍተው ስራው ተጠናቆ የከተማውና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡ በርክክብ ወቅትም  የፕላነር ባለሙያዎች  አቶ አብዱ ሰይድና አቶ ሰኝ መርጋ ፕላኑን በተመለከተ ለከተማው አመራሮች  ሰፊ ማብራርያ  ሰጥተዋል፡፡ በርክክቡ ወቅት የተገኙ አመራሮችም በፕላኑ መሰርት ስራውን ለመስራት የበጀት እጥረት ቢኖርም በቁረጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ አክለውም ወደ ስራው ስንገባ ለሚፈጠሩ ችግሮችም  የክልሉ ቢሮ ድጋፍ ማድረግ አለባችሁ ብለዋል፡፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተማ ፕላን ጽዳትና ውበት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደስታው ወርቁ የተሰራው ፕላን ለ10 አመት የሚያገለግል ስለሆነ በጥንቃቄ መሰራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ አክለውም በአፈጻጸም ወቅት ለሚፈጠሩ አንዳንድ ችግሮች ቢሮው በቅርበት ክትትል በማድረግ ድጋፉን አጠናክሮ የሚሄድ መሆኑን ገልጸው የከተማውና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም የመንጌ ከተማ መሰረታዊ ፕላን ቀደም ስል ከተሰራው ፕላን ላይ የተለያዩ ማሻሻያዎችን ተጨምሮበት ስራው ተሰረቷል፡፡  በዚህ ላይም የተደረጉ ማሻሻያዎችን በተመለከተ የፕላን ባለሙያዎች  አብራርተው በሰፊው ተወያይተዋል፡፡  የከ/ፕ/ጽ/ው ዳይሬክተሩ አቶ ደስታው ወርቁ ፕላኑ ለ10 አመት የሚያገለግል በመሆኑ ስራውን በአግባቡ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡ አክለውም ፕላኑ ከተረከባቹበት ቀን ጀምሮ ወደስራው መግባት አለባችሁ ብለዋል፡፡ ስራውን ሲሰራ ለሚፈጠረው አንዳንድ ችግሮች ክትትልና ድጋፊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ የመንጌ ማዘጋጃ ስራ አስካጁም ስራዎች ላይ አንዳንድ አመራሮች ጣልቃ ሲለሚገቡ ቢሮው ሊከታተለን ይገባል ብለዋል፡፡ 

በተመሳሳይም የሆሞሻ ከተማ መሰረታዊ ፓላን ርክክብ  ተደርግል፡፡ በርክክቡ ላይም የከተማው አመራሮች የተገኙ ሲሆን ፕላኑን በተመለከተ የፕላን ባለሙያዎች በሰፊው አብራርተዋል፡፡

የተገኙት አመራሮችም ፕላኑ ለ10 አመት የሚያገለግል ስለሆነ በጋራ ተናበን የሚንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ እንዲሁም አመራሩ በቁርጠኝነት ወደስራ በማስገባት በፕላኑ መሰረት ስራውን መስራት አለብን ብለዋል፡፡ አክለውም ስራውን ስንሰራ በሚገጥሙን ችግሮች ሲኖሩ የክልሉ ባለሙያዎች ጋር በጋራ መስራት አለብን ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፕላኑን የሰሩ ባለሙያዎችንና ቢሮውን አመስግነዋል፡፡

የከ/ፕ/ጽ/ው/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተረ አቶ ደስታው ወርቁ ወደስራው ስትገቡ የሚፈጠሩ ችግሮች ሲኖሩ ቢሮው ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አክለውም ፕላኑ ለ10 አመት የሚያገለግል ስለሆነ ስራውን በቁርጠኝነት መሰራት እንደሚገባቸው ለሶስቱም የከተማ አመራሮች አሳስበዋል፡፡

ከሆሞሻ ከተማ ፕላን የቅየሳ ስራው በ2012 የተጀመረ ሲሆን 158 ብሎኮች ተከፍተው በ2013 በጀት አመት መጀመሪያ ላይ  ስራው ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡ በአጠቃላይ የሶስቱ ከተሞች የመሰረታዊ ፕላን ርክክብ ተደርጓል፡፡ በማለት የዘገበው የቢሮው ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ክፍል ነው፡፡

Chat
Minimize Maximize
Chat is temporarily unavailable.