Organization Structure Organization Structure
Minimize Maximize

የክልሉ መንግስት በ 1987 ዓ/ም በአዋጅ ከአቋቋማቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አንዱ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ነው ፡፡ የተቋቋመበት ዓላማም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ሥርዓት ባለው መንገድ እንዲሰሩ በማድረግ የከተሞች ልማትና ዕድገትን ለማፋጠን ሲሆን ይህንን ዓላማ ለማስፈፀም በዓዲሱ የሥራ አሠራር ሂደት መሠረት በሰባት ዋናወና የሥራ ሂደቶች ተደራጅቷል ፡፡

በ 2003 ዓ/ም የቢሮውን ዓላማ ያሳካል ተብሎ ታምኖበት አዲስ በተቀረፀው የአሠራር ሂደት ለውጥ ተሸሽሎ በወጣው ድርጅታዊ መዋቅር መሠረት የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ቢሮ በሥሩ ሰባት የሥራ ሂደት ባለቤቶች እና በሥራቸው የሚገኙ ደጋፊ የሥራ ሂደት ኦፊሰሮች እንዲቋቋሙ ተደርጓል ፡፡

የቢሮው የትኩረት አቅጣጫና የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

1.  የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሠረታዊ አሰራር ሂደት ለውጥ በተቀናጀ መንገድ ሥራ ላይ በማዋል የከተሞች ልማት እንዲፋጠን ምቹ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

2.  የከተማ ልማትና ቤቶች አዋጅ፣ ፖሊሲዎችና ደንቦች መመሪያዎችን በክልል ውስጥ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

3.    ከተሞች መሪ ፕላን ኖሯቸው የከተማው ልማት እንዲፋጠን ያደርጋል ፡፡

4.  በከተሞች የመኖሪያ ቤቶች ችግር ለማቃለል ቤቶች እንዲሰሩና ሁሉም ዜጋ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ምቹ ሁኔታ ያመቻቻል፤ በከተሞች ደረጃቸውን የጠበቁና ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመጥን የቤት ልማት ሥራ ለማከናወን ልዩ ትኩረት ይሰጣል ፡፡ ማለትም ለመኖሪያና ለመስሪያ የሚሆን ቦታ ለሁሉም በተቀናጀ መልኩ ማቅረብ ሲሆን ትኩረቱ የቁጠባ ቤቶችን እንዲስፋፋ ማገዝ ነው ፡፡  እገዛውም የለማ መሬትን በማቅረብ አማራጭ ዲዛይንና የግንባታ ቴክኖሎጂ በማቅረብ ወይም የሚያቀርቡትን በማበረታታት ዙሪያ ይሆናል ፡፡

በአጠቃላይ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ይሁን እንጅ ሙሉ በሙሉ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ ብዙ ችግሮች ያጋጥሙታል ፡፡ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ዋናዋናዎቹ ናቸው ፡፡

1.. የመንግስት ኪራይ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ በፌደራል ደረጃ በጀትም ሥላልተሰጠ ቤት ፈላጊውን ህብረተሰብ ፍላጎቱን ማርካት አልተቻለም ፡፡

2. ነዋሪውን ህብረተሰብ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተሰጥቶት የራሱን እንዳይሰራ በክልሉ ባለው ነባራዊ ሁኔታ መንግስት አለኝ የሚለውን የመሬት ሃብት ከብዝበዛ ለማዳን ሲባል መንግስትም ይህንኑ ሃብት ከወራሪዎች ለመታደግ በዘረጋው ምቹ አሰራር ማለትም የመሬት ሊዝ ስሪትን ለመተግበር ወደ ክልሉ ሲያወርድ የሚመለከታቸው አካላት ባለባቸው የሰው ኃብት ውስንነት እና የውሳኔ መጓተት ምክንያት ለቦታ ፈላጊዎች በሚፈለገው ጊዜ ቦታ ሊሰጣቸው አለመቻል ፡፡

3. በክልሉ ያሉት አንዳንድ ኮንትራክተሮች የግንባታ አፈፃፀም አቅማቸው ዝቅተኛ መሆንና ወደ ግንባታ ሲገቡ ተገቢውን ክትትል ስለማይደረግባቸው

4. የመ/ቤታችን የምህንድስና ክፍል በተፈላጊው ሰዓት ወደ መስክ ሂደው ግንባታዎችን እንዳይከታተሉ እና እንዳይቆጣጠሩ ለዚሁ ሥራ ማስፈፀሚያ የሚሆን በጀት አስካሁን ባለመመደቡ ግንባታዎች በተፈለገው ጊዜ አለመጠናቀቅ ዋና ዋናዎቹ ችግሮች ሲሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን ችግሮች ለመቅረፍ ለ 2006 ዓ/ም ከወዲሁ ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡