Message Message
Minimize Maximize


የከተማ ልማት ቤቶችችና ኮንስትራክሽ  ቢሮ ኃላፊ መልዕክት

የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ሲታቀድ ኢኮኖሚያችን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ሊሸጋገር የሚችልበትን አግባብ በግልፅ አስቀምጦ ርብርብ እየተደረገበት ይገኛል፡፡ ኢኮኖሚያችን ኢንዱስትሪ መር ይሆናል ሲባል የግብርናው እድገት ይቋረጣል ማለት ባይሆንም የኢንዱስትሪ ድርሻ በላቀ ፍጥነት ያድጋል ማለት በመሆኑና ስለ ኢንዱስትሪ ዕድገት ሲታሰብ ደግሞ በአነስተኛ ካፒታልና የመሬት አቅርቦት ሰፊ የሰው ኃይል ሊያንቀሳቅስ የሚችለውን የጥቃቀንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ትኩረት በመስጠት መስራት የሚጠይቅ መሆኑን በግልጽ የተቀመጠ ነው፡፡

በጥቃቅንና አነስተኛ የሥራ ዘርፎች የሚፈጠሩት ኢንዱስትሪያሊስቶች በምንፈልገው መንገድ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉት የሚኖራቸው ለማምረቻና መሸጫ የሚሆን በቂ መሬት በአግባቡ ሲቀርብባቸውና ሠፊና ጥራት ያለው ምርት አምርተው በገበያ በመወዳደር ብቻ ተጠቃሚ እንሆናለን የሚል ጠንካራ ልማታዊ አስተሳሰብ እንዲይዙ በየዕለቱ የሚታይባቸውን የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር እየታገሉ ማስተካከለ ሲቻል ነው፡፡

የምንፈልገውን ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በመገንባት  የአገራችን ዕድገትና የህዝቦችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የመሬት አስተዳደራችን ግልፅና የህዝብን ጥቅም የሚያስጠብቅ ለማድረግ የከተማን ቦታ በሊዝ የመያዝ አዋጃችን በተሟላ መንገድ ተፈፃሚ በማድረግ መሬት በምደባና በጨረታ ስርዓት ብቻ የሚተላለፍበትና በእውነተኛ ዋጋው የሚቀርብበት፣ ዜጐች ለዘመናት የያዙትን መሬታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙበትና ህገወጦች በወረራ መሬት እየያዙ እንዲቀጥሉ የማይፈቀድበትን የአሰራር ስርዓት የማረጋገጥ ሥራ ልንሠራ ይገባል፡፡

በኢንዱስትሪው ዘርፍ ለተሰማራው ኃይል እንደየአግባቡ መሠረተ ልማት የተሟላለት መሬት በማቅረብ፣ አቅሙን መሠረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል በማድረግና ምቹ የገበያ ዕድል በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲያረጋግጥ መስራት የማይታለፍ እውነታ ነው፡፡

በከተሞች የልማት ሠራዊት ይገነባል ተብሎ የሚታመነውና እየተሠራም ያለው በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በትምህርትና  በሰቪል ሰርቪስ ተቋማት ሲሆን ከኛ ተልዕኮ አንፃር በሰቪል ሰርቪሱ ተቋም ያለውን ፈጻሚ በጠንካራ የልማት ሠራዊት ከተገነባና በዚሁ የሚመራ ከሆነ ራሱን ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር አጽድቶ  በእጁ ላይ ያለውን የህዝብ ሀብት (መሬት) በአግባቡ ልማት ላይ እንዲውል ያደረገዋል፣ የኢኮኖሚውን ተዋናዮችን በአግባቡ ይከታተላል፣ ይደግፈል፣ ውጤታማ ያደረገ በመሆኑም የኛ የወቅቱ ተልዕኮ ጠንካራ የልማት ሠራዊት መገንባት መሆኑን አምነን ለዚሁ ስኬት በሰፊው በማቀድ መተግበር ይኖርብናል፡፡

 

 

Document Library Display Document Library Display
Minimize Maximize
Showing 18 results.
Showing 18 results.

Cities Cities
Minimize Maximize

 

Chat
Minimize Maximize
Chat is temporarily unavailable.